የሶማሊያ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በነበራቸው በቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂዮ ሜሎኒ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሁለቱ ሀገራት መሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት የሶስትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
መሪዎቹ በመሰረተልማትና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራታቸውን አጠናክረው መቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡