Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ጋርተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከሱዳን አምባሳደር ጀማል ኤል ሼክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በትኩረት መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ÷ በሱዳን  ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ኢትዮጵያን በእጅጉ  እንዳሳሰባት ተናግረዋል፡፡

በሁለቱ ወንድማማች ፓርቲዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት በውይይት እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

የተከሰተውን ችግር በሱዳናውያን አቅምና ችሎታ በሰላማዊ ውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎች እና ዲፕሎማቶች አስፈላጊ ጥበቃ እንደሚያገኙ እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.