Fana: At a Speed of Life!

4ኛ ቀኑን በያዘው የሱዳን ግጭት 200 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

ግጭቱ የሱዳን ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን በሚመሩት የሱዳን ጦር እና ምክትላቸው መሃመድ ሀምዳን ደጋሎ (ሄምቲ) በሚመሩት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል ነው እየተደረገ የሚገኘው፡፡

አራተኛ ቀኑን በስቆጠረው በዚህ ግጭትም እስካሁን 200 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በሱዳን የተመድ ልዩ ተወካይ ቮልከር ፔርቴስ እንደተናገሩት÷ እስከ ትናንት ድረስ ባለው መረጃ ለህልፈት ከተዳረጉ ዜጎች በተጨማሪ 1 ሺህ 800 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በሱዳን በሁለቱ ወንድማማች ፓርቲዎች መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በጥብቅ ማውገዛቸውን ሲ ጂቲ ኤን ዘግቧል፡

የተለያዩ ሀገራት መሪዎችም ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች የጀመሩትን ግጭት በማርገብ ችግሩን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.