Fana: At a Speed of Life!

ሀንጋሪ ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ዘርፍ ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀንጋሪ ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ዘርፍ ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቃለች።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከሀንጋሪ የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስትር ፒተር ሲያርቶ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት በከፍተኛ ትምህርት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሀንጋሪ ለኢትዮጵያውያን የምትሰጠውን የትምህርት እድል ማስፋት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር የተደረገ ሲሆን÷ እድሉን በእጥፍ እንደምታሳድግም አስታውቃለች።

በዚህም በየዓመቱ ለ50 ኢትዮጵያውያን ይሰጥ የነበረውን የትምህርት እድል ወደ 100 ከፍ ማድረጓን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.