Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የህዝቡን ሰላም በማረጋገጥ ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር ማድረግ እንደሚገባ አስገነዘቡ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰላም የሁሉም መልካም ነገር መሠረት እንደመሆኑ ያለ ሰላም ልማት የማይታሰብ መሆኑን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም “ሕዝባችን ሰላሙን በማረጋገጥ ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር የማድረግ የጋራ ኃላፊነት አለብን” ብለዋል።

በነቀምቴ ለነበራቸው ቆይታ እና ውይይትም ሕዝቡን አመስግነዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.