ሕንድ በሕዝብ ብዛት ቻይናን በመብለጥ ከዓለም ቀዳሚ ሆነች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ሕንድ በሕዝብ ብዛት ቻይናን በመብለጥ ከዓለም ቀዳሚ መሆኗን የተመድ የዓለም የሥነ-ሕዝብ ልኬት መረጃ አመላከተ፡፡
የሕንድ ሕዝብ 1 ነጥብ 42 ቢሊየን ገደማ መድረሱን “ወርልድ ኦ ሜትር” እና የተመድ የሥነ-ሕዝብ ልኬት መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
ቻይና ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን በላይ ሕዝብ ያላት ሲሆን 900 ሚሊየን ገደማው ዕድሜያቸው ለሥራ የደረሰ መሆኑን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡
በቻይና የአረጋውያን ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በመውለድ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ቻይናውያን እስከ ሦስት ልጅ እንዲወልዱ የሚያበረታታ ብሔራዊ ስትራቴጂ አፅድቃ እየተንቀሳቀሰች ነው ተብሏል፡፡
በተያያዘ መረጃ ከትናንት በሥትያ የሕንድ መንግስት በሙምባይ ባዘጋጀው የሽልማት መርሐ-ግብር ላይ ለሠዓታት ታዳሚ ከነበሩት ሰዎች መካከል 11ዱ በፀሐይ ሙቀት እና በመጨናነቅ ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።