ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ውጥረት ረግቦ ሰላም እንዲሰፍን የሔድንበት መንገድ ውጤታማ ነው አሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የናይጀሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የነበረውን ውጥረት ለማርገብ የሄድንበት መንገድ ውጤታማ ነው ሲሉ ገለጹ፡፡
በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር 2021 ገና ለዚህ የሰላም ማስፈን ሥራ ስሰለፍ ውጥረቱ ረግቦ ሰላም እንደሚሰፍን ሙሉ ተስፋ ነበረኝ ብለዋል በንግግራቸው፡፡
በኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በህወሓት በኩል ለሰላም ሂደቱ መሳካት የነበረው አዎንታዊ አቀባበል ለሰላም ማስፈን የተደረገውን ጥረት በእጅጉ ያገዘ እንደነበርም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
የሰላም ሂደቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ያሳየውን ቁርጠኛነት አድንቀው ለስምምነቱ ውጤታማነት እና ዘላቂነት ትልቅ ማሳያ ስለመሆኑም ነው የተናገሩት፡፡
በጠፋው ሕይወት ብናዝንም ነገር ግን በተገኘው ሰላም ደግሞ ደስታችንን እንገልፃለን ብለዋል፡፡
በሰላም ስምምነቱ መሠረት የተከናወኑ ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቀሪ ሥራዎችም በፍጥነት እንዲፈጸሙ ጠይቀዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!