አቶ ደመቀ መኮንን በዛንዚባር የሚገኘውን የአፄ ኃይለሥላሴ ትምህርት ቤት ጎበኙ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በዛንዚባር የቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ገብኝተዋል።
ትምህርት ቤቱ ከ75 ዓመታት በፊት መመስረቱ በጎብኝቱ ወቅት ተገልጿል።
የትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች በወቅቱ እንደገለፁት የታንዛኒያ መስራች አባት ጁሊየስ ኔሬሬ ትምህርት ቤቱን በአፄ ኃይለስላሴ ስም የሰየሙት ንጉሱ ለአፍሪካውያን ነፃነት ለነበራቸው አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት ነበር።
አቶ ደመቀ መኮንን በዚህ ወቅት በክብር መዝገብ ላይ ባሳፈሩት ማስታወሻ የአሁኑ ትውልድ የአፍሪካ መስራች አባቶችን ፈለግ በመከተል ተባብሮ መስራት አለበት ብለዋል።
በጉብኝታቸውም የመታሰቢያ ችግኝ በቅጥር ግቢው ተክለዋል።