Fana: At a Speed of Life!

ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችን ግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአማራ ክልል ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት ግርማ የሺ ጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል ብለዋል።

ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው ሲሉም ነው የገለጹት።

ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው ብለዋል።

ነፍሳቸው በሰላም እንድታርፍም ተመኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.