Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በአቶ ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል።

አስተዳደሩ በሃዘን መግለጫው÷አሁን ያለንበት ወቅት የትኛውንም የፖለቲካ አመለካከት በነፃነት ማራመድና የሃሳብ ትግል  ማድረግ የሚቻልበት ጊዜ ነው ብሏል።

ነገር ግን የፓለቲካ ትግሉን በዕውቀትና በእውነት ማራመድ የተሳናቸው ማሰብ የሚችሉ ባለ ብሩህ ራዕይ ሰዎችን ማጥቃት ብቸኛ አማራጫቸው አድርገውታል ሲልም ገልጿል።

በዚህ ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ማሳያ መሆኑን አንስቷል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው የአማራ ክልል ህዝብ መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.