የአፍሪካ ሕብረት ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለሱዳን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያቀርብ ጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረት በሱዳን ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለማቃለል አስቸኳይ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ጠየቀ፡፡
እንዲሁም ግጭቱን ሸሽተው ከሱዳን ለሚወጡ ሰዎችም ጎረቤት ሀገራት እና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ አስፈላጊውን ሁሉ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው የተጠየቀው፡፡
በሱዳን ያለውን ግጭት ሰላማዊ ዜጎችን ችግር ላይ ይጥላል በሚል ስጋት ሥጋት እየተከታተሉት መሆኑን የአፍካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ገልጸዋል፡፡
የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎችም በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡