Fana: At a Speed of Life!

የኒጀር፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያና ኮትዲቩዋር የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኒጀር፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያና ኮትዲቩዋር ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን ለመጎብኘት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የልኡካን ቡድኑ አባላት ከኒጀር፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያና ኮትዲቩዋር የተውጣጡ የግብርና፣ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት፣ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይና ሌሎች ተቋማትን የወከሉ ሚኒስትሮችና ሌሎች የስራ ኅላፊዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።

በኢትዮጵያ ለአራት ቀናት በሚያደረጉት የስራ ጉብኝትም የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ይመለከታሉ መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.