Fana: At a Speed of Life!

በአደገኛ ዕፅ ዝውውር የተጠረጠረው ጋዜጠኛ በቁጥጥር ሥር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአደገኛ ዕፅ ዝውውር የተጠረጠረውን ጋዜጠኛ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

በአደገኛ ዕፅ ዝውውር የተጠረጠረው ጋዜጠኛ በቁጥጥር ስር የዋለው ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ ዕፁን ለማስተላለፍ ሲል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በዚህም ከጉዞ በፊት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ  በሚያደርገው የሰው አካልና የሻንጣ ፍተሻ በተጠርጣሪው የጉዞ ሻንጣ አካል ውስጥ ተሰርቶ ሊያልፍ የነበረ በዱቄት መልክ የተዘጋጀ 2 ነጥብ 10 ኪሎ ግራም ኮኬይን አደገኛ ዕፅ ከተጠርጣሪው ጋዜጠኛ ጋር ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ40 መያዙ ታውቋል፡፡

በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተገለፀ  ሲሆን÷ ግለሰቡ ከአሁን በፊትም ወደ ተለያዩ ሀገራት በሰዎች አማካኝነት አደገኛ ዕፅ ይልክ እንደነበር የፖሊስ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳይ ተገልጿል።

በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተገለፀ  ሲሆን÷ ግለሰቡ ከአሁን በፊትም ወደ ተለያዩ ሀገራት በሰዎች አማካኝነት አደገኛ ዕፅ ይልክ እንደነበር የፖሊስ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳይ  መገለፁን ከፌደራል  ፖሊስ  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.