Fana: At a Speed of Life!

ሞስኮ በክሬሚሊን አቅራቢያ ሲበሩ ነበሩ ያለቻቸውን የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች መትታ መጣሏን ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሞስኮ ክሬሚሊን በሚገኘው የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቤተ መንግሥት አቅራቢያ ሲበሩ ነበሩ ያለቻቸውን የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች መትታ መጣሏን ገለፀች።

በክሬምሊን አቅራቢያ ትናንት ምሽት ሲበሩነበሩ የተባሉት ሁለቱ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በፕሬዚዳንት ፑቲን ላይ ጥቃት ለማድረስ ነበር ተብሏል፡፡

የፕሬዚዳንት ፑቲን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለሀገሪቱ የዜና ምንጭ እንደተናገሩት ÷ በወቅቱ ፕሬዚዳንቱ በቤተ መንግሥታቸው አልነበሩም፡፡

በሕንጻዎቹ ላይም የደረሰ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመኖሩንም ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሞስኮ ሰው አልባ አውሮፕላኖቹን ልዩ የኤሌክትሮኒክ ራዳር ሞገድ በመጠቀም መጣሏንም ነው ያስታወቀችው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.