Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በጅቡቲ በሚገኙ ኢትዮጵያውን እና ተመላሽ ስደተኞች ጉዳይ ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በጅቡቲ በሚገኙ ኢትዮጵያውን እና ተመላሽ ስደተኞች ጉዳይ ዙሪያ ተወያዩ።

አምባሳደሩ ከጅቡቲ የሃገር ውስጥ ሚኒስትር ሰይድ ሃሰን ጋር ባደረጉት ውይይት፥ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ መምከራቸውን አስታውቀዋል።

በዚህ ወቅትም ሚኒስትሩ በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ሰብአዊ መብት እና ክብር ለማስጠበቅ መንግስታቸው ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸውላቸዋል።

በተጨማሪም ከዜጎች አያያዝ ጋር በተያያዘ የሚያደርጉትን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸውንም ጠቅሰዋል።

አምባሳደሩ በጅቡቲ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ሃላፊ ታንያ ፓሲፊኮ ጋርም ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም በጅቡቲ የሚገኙና ፈቃደኛ ተመላሽ ዜጎችን በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸውን ነው የገለጹት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.