ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ተመለሱ።
መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ እና ኬንያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ በዛሬው እለት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
በቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ከእርሳቸው ጋር ወደ ኢትዮጵያ የመጣ የጀርመን ልዑካን ቡድንም ከተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይቷል።