Fana: At a Speed of Life!

ዲጂታል የነዳጅ ግብይት ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መደረግ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁሉም ክልሎች የዲጂታል የነዳጅ ግብይትን በሲቢኢ ብር እና ነዳጅ መተግበሪያ ማስጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ዛሬ በአዳማ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ሃላፊዎች እና የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ ሃላፊዎች ተገኝተው አስጀምረዋል።

የነዳጅ ግብይቱ የሚከናወናው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲቢኢ ብር እና ነዳጅ መተግበሪያ እንደሆነ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደረጀ ፉፋ÷የነዳጅ ግብይቱ በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት መሆኑ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው ሀብት ለታለመለት ዓላማ ለማዋል ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

ነዳጅ ለመቅዳት የሚታየውን ሰልፍና እንግልት እንደሚያስቀርም ገልጸዋል።

ዲጂታል የነዳጅ ግብይት አገልግሎቱ በሲቢኢ ብር እና ነዳጅ መተግበሪያ አማካኝነት ከ1 ሺህ ማደያዎች በላይ ተግባራዊ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጎሹ በበኩላቸው÷ ዛሬ በክልሉ የተጀመረው ዲጂታል የነዳጅ ግብይት አገልግሎት ነዳጅ ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ በአግባቡ እንዲደርስ የሚያስችል ነው ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.