አቶ ደስታ ሌዳሞ ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በተያዘው በጀት ዓመት እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን አፈፃፀምና በቀጣይ ዓመት ሊሰሩ በታቀዱ ሥራዎችን ላይ መክረዋል፡፡
አቶ ደስታ ÷ አመራሩ የከተማዋ ገቢ እንዲያድግ፣ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል፣ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲሁም ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ዕቅድ መሰረት እንዲፈጸሙ አሳስበዋል፡፡
ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ እንዲቆም እና የዋጋ ንረትን ሊያረጋጋ የሚችል ሥራ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ መመሪያ መስጠታቸውንም የርዕሠ-መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡