አየር መንገዱ በቦሌ ክፍለ ከተማ በመጠለያ ውስጥ ለሚገኙ 400 ዜጎች ለ15 ቀናት የምሳ ምገባ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ክፍለ ከተማ በመጠለያ ውስጥ ለሚገኙ 400 ዜጎች ለ15 ቀናት የሚቆይ የምሳ ምገባ መርሃ ግብር አስጀመረ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ አየር መንገዱ አስቸጋሪ ጊዜን እያሳለፈም ቢሆን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ግን ወድ ኋላ አይልም ብለዋል።
ኢትዮጵያዊ አንድነትን ከምንግዜውም በላይ ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተወልደ፥ ድጋፉ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይሆንም ብለዋል።
በዛሬው እለት የተጀመረው የምሳ ምገባ መርሃ ግብር ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ይካሄዳል።
ድጋፉ የተደረገላቸው ዜጎች በቦሌ ክፍለ ከተማ በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
በዛሬው ድጋፍም የንጽህና መጠበቂ ቁሳቁሶችም ድጋፍም ተደርጓል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በበኩላቸው፥ አየር መንገዱ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ማዕዳችንን እናጋራ በሚል ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።
በምስክር ስናፍቅ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።