በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
በ24 ሰአታት ውስጥ ለ1 ሺህ 80 ሰዎች ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ገልፀዋል።
ሚኒስትሯ በተደረገው ምርመራም ተጨማሪ 2 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የገለፁ ሲሆን፥ ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 126 ደርሷል ብለዋል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁለቱም ሰዎች የ42 ዓመት እና የ50 ዓመት እድሜ ያላቸው የብሪታኒያ ዜጎች ሲሆን፥ በቅርቡ ከብሪታንያ የመጡ እና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የቆዩ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 126 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 71 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ፤ 50 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸው ይታወቃል።