Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሞ ምሁራን ምርምር ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ምሁራን ምርምር ስራዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በውይይት መድረኩ የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ሃደ ሲንቄዎች፣ ምሁራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ የኦሮሞን ሕዝብ ባህል፣ ቋንቋ ፣ታሪክ እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ የምርምር ግኝቶች ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

የውይይት መድረኩን የኦሮሞ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲትዩት እና ሲንቄ ባንክ በጋራ ያዘጋጁት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.