Fana: At a Speed of Life!

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጉብኝት እያደገ የመጣውን የሁለቱ ሀገራት ትስስር የሚያመለክት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት እያደገ የመጣውን የሁለቱ ሀገራት ትስስር የሚያመለክት ነው አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡
ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል እያደገ የመጣውን ትስስር የሚያመለክት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ውይይቶቻችን በጋራ የቅድሚያ ጉዳዮቻችን ላይ ትብብሮቻችንን የበለጠ የምናጠናክርበት እንደሚሆን እምነቴ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.