Fana: At a Speed of Life!

በኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራ ልዑክ ጅቡቲ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እና የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ፕሬዚዳንት ጄኔራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል የተመራ ልዑክ ማምሻውን ጅቡቲ ገባ፡፡

ልዑኩ ወደ ጅቡቲ ያቀናው የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ የተመሰረተበትን 46ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ መሆኑን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት ጅቡቲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በጅቡቲ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሰደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.