Fana: At a Speed of Life!

በአዳጊ ሀገራት ያለውን የዓየር ንብረት ፋይናንስ ጉድለት መሙላት ይገባል- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የዓየር ንብረት ለውጥ ለፈጠራቸው ተግዳሮቶች ምላሽ ለመስጠት በአዳጊ ሀገራት ዘንድ ያለውን የዓየር ንብረት ፋይናንስ ጉድለትን መሙላት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉዳዩ ላይ ባወጡት መልዕክት ኢትዮጵያ የዓየር ንብረት ለውጥ ግንባር ቀደም ተጠቂ መሆኗን አመልክተዋል።

ለውጡ ባመጣው የከፋ የዓየር ሁኔታ እና ድርቅ የዜጎችን የምግብ እና የውሃ ዋስትና እየተፈታተነው እና የሀገሪቱን እድገት እየጎዳው መሆኑን ነው የጠቆሙት።

ለእንዲህ ዓይነቱ ተግዳሮት ምላሽ ለመስጠትም በ27ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ቃል የተገባውን የፋይናንስ ድጋፍ ለተጎጂ ሀገራቱ በመስጠቱ ተጨባጭ እርምጃ ያስፈልጋል ብለዋል።

28ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን የምታስተናግደው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሚመለከታቸው አካላት እነ በሀገራት መካከል መግባባትን በመፍጠር ከጉባኤው ተጨባጭ ውጤት እንደምታስገኝ ሙሉ እምነት እንዳላቸውም ነው የጠቆሙት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.