2ኛው ዙር ሀጫሉ አዋርድ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀጫሉ ፋውንዴሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ሁለተኛው ዙር ሀጫሉ አዋርድ እየተካሄደ ነው።
ባለፈው ዓመት በ10 ዘርፎች የተካሄደው አዋርዱ ÷ዘንድሮ በ12 ዘርፎች ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
ከዘርፎቹ ውስጥ የዓመቱ ምርጥ አልበም፣ ዘፈን፣ አቀናባሪ፣ ባህላዊ ዘፈን፣ አዲስ ወንድ ድምጻዊ፣ አዲስ ሴት ድምጻዊ፣ የሙዚቃ ቪዲዩ ክሊፕ፣ የሙዚቃ ቪዲዩ ኤዲተር እና ባህላዊ ኬሮግራፊ ይገኙበታል።
ከመጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም የወጡ የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎች ለውድድር መቅረባቸው ተመላክቷል፡፡
ውድድሩ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ህልም እና አላማ ለማሳካት ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
የህይወት ዘመን ተሸላሚ አርቲስት አቡበከር ሙሳ ሆኖ ሲመረጥ ÷በባህላዊ ኬሮግራፊ ዘርፍ ደግሞ ሽመልስ አለሙ እና ቱሉ ሂርጶ አሸንፈዋል።
በሌላ በኩል በሙዚቃ ቪዲዩ ኤዲተር ሊዩስ አባ ቦንቲ ሲያሸንፍ÷በቪዲዮ ክሊፕ ዘርፍ ደግሞ ብሩክ ግርማ አሸንፏል።
በፍቅርተ ከበደ