ከንቲባ አዳነች የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ 8 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና ከ10 እስከ 40 ሜትር የጎን ስፋት ያለው የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ ፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ህዳር 2013 ዓ.ም የመንገዱን ግንባታ ባስጀመርንበት ወቅት የአካባቢው መህበረሰብ እና የጋራ መኖርያ ቤት ባለዕድለኞች “ቶሎ ገንቡልን” ሲል ጋቢ አልብሰው አደራ ሰጥተውን ነበር ብለዋል።
በዚህም መሰረት መንገዱ በአካባቢው ያለውን የመንገድ መሰረተ ልማት እጥረት የሚቀርፍ እና የጋራ መኖርያ ቤት ባለዕድለኞች ወደ ቤታቸው ሲገቡ የሚሰጣቸውን ፋይዳ በመገንዘብ ግንባታው በተጀመረበት ወቅት በተገባው ቃል መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዚህ በጀት አመት የተያዙ ትልልቅ ተሻጋሪ ድልድዮች እና የመንገድ ፕሮጀክቶችም እየተጠናቀቁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡