የብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት የእውቅና እና የሽልማት መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ ወጣቶች የእውቅናና የሽልማት መርሃ- ግብር በአዳማ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡
እውቅናው አገልግሎቱ ከተጀመረ አንስቶ በሰባት ዙሮች ለተሳተፉ ከ42 ሺህ 500 በላይ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የተዘጋጀ ነው ተብሏል።
የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ታዬ ደንደአ÷ብሔራዊ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ወጣቶች ለህዝብና ለአገር ፍቅር ቅድሚያ በመስጠት የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ነው ብለዋል።
መርሐ ግብሩ ወጣቶቹ ተልዕኳቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን ለመግለጽ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ህይወታቸው በተለያዩ ተመሳሳይ አገልግሎት ተሳታፊ እንዲሆኑ አደራ ለመስጠትም ጭምር እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡