Fana: At a Speed of Life!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 6ኛውን፣ 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 28ኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡

ምክር ቤቱ በስብሰባው የ27ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔን መርምሮ አጽድቋል፡፡

የምክር ቤት አባላትም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌደራል መንግስት የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ምክር ቤቱ በውሎው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት በጀትን አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን አጽድቋል፡፡

በየሻምበል ምሕረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.