Fana: At a Speed of Life!

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለጤና መስክ  ተማሪዎች የመውጫ ፈተና  መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ2015 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለጤና መስክ  ተማሪዎች  መስጠት ጀምሯል።

የመውጫ ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ በቀጥታ በበይነ መረብ ከማዕከል እየተሰጠ ሲሆን ÷የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱረህማን ከድር( ዶ/ር ) በፈተና ጣቢያዎች በመገኘት ፈተናውን አስጀምረዋል፡፡

ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ከግል ኮሌጆች እና ከጤና ሚኒስቴር የተመደቡ በጠዋቱ ፈረቃ 304 ፣ ከሰዓት በኋላ 277 በአጠቃላይ 581ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡

ተፈታኞቹ  የጠዋቱን  ፈተና ያለምንም ችግር በጥሩ የፈተና ድባብ በማገባደድ ላይ እንደሚገኙም ነው የተገለጸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለ 1ሺህ 939 መደበኛ እና የማታ  ተማሪዎቹ እንዲሁም  850 በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን የግል ትምህርት ተቋም ተማሪዎችን ጨምሮ በጠቅላላ 2 ሺህ 789 ተማሪዎችን የመውጫ ፈተና እንደሚያስፈትን  ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.