Fana: At a Speed of Life!

ስንዴን በኩታ ገጠም እርሻ በማምረት ከውጭ የሚገባውን ምርት የመተካት አቅም አለ – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስንዴን በኩታ ገጠም እርሻ በማምረት ከውጭ የሚገባውን የስንዴ ምርት የመተካት አቅም መኖሩን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ጂዳ ወረዳ በመስኖ ልማት 2 ሺህ 800 ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም መታረሱ ተስፋ ሰጭ ውጤት ማስገኘቱን በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

ይህም በሀገር ደረጃ ምርታማነት በዚህ መልኩ ካደገ ስንዴን ከውጭ ማስገባት ታሪክ ሆኖ እንደሚቀር ማሳያ ነው ብለዋል።

በዚሁ ወረዳ በወጣቶች እየተካሄደ ያለው የከብት ማድለብ ሥራም ተስፋ የሚጣልበት መሆኑንም ገልጸዋል።

አያይዘውም በመላ ሃገሪቱ የሚገኙ አነስተኛ የመሬት ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ድጋፍ እየተደረገላቸው ይህን አቅም በመገንባት ላይ እንዲያተኩሩም መልዕክት አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.