አቶ ደመቀ መኮንን ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብሽር ኦማር ጃማ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ በኬንያ እየተካሄደ ከሚገኘው 43ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡
ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው÷ በሁለትዮሽ እና አከባቢያዊ ጉዳዮች እንዲሁም በሀገራቱ ወቅታዊ ወዳጅነትን ዙሪያ መክረዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሁሉም መስኮች የተሳሰሩ መሆናቸው በውይይቱ መገለጹን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በሀገራቱ የጋራ ጉዳዮች ይበልጥ ተባብረው ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውንም ሚኒስትሮቹ አረጋግጠዋል፡፡