Fana: At a Speed of Life!

አቶ መላኩ አለበል ሩሲያ ከሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ሩሲያ ከሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች እና ኢንትርፕራይዞች አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ከማዳበሪያ፣ ኬሚካል ኢንጂነሪንግ፣ ትምህርት፣ ስፔስ ሮኬት ምህንድስና፣ ሕክምና መሳሪያ የተውጣጡ የአምራች ኢንዱስትሪዎችና ኢንተርፕራይዞች አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንነኙነት ላይ አዎንታዊ ሚና እንደሚጫዎት አቶ መላኩ ተናግረዋል፡፡

በግብርና እና ማዳበሪያ፣ በፔትሮሊየም፣ በትምህርት፣ በአየር ትራንስፖርት ስምምነት እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዙሪያ ያለው ትብብር ላይ በትኩረት መምክራቸውንም አንስተዋል፡፡

ሚኒስትሩ “ጄ ኤስ ሲ ኡራለሂማሽ” የተሰኘ ኩባንያን የጎበኙ ሲሆን÷ በዚህም የኬሚካልና የብረታ ብረት ውጤቶችን ተመልክተዋል፡፡

ከኡራል ፌዴራል ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ጋርም በዩኒቨርሲቲው ስላሉት የትምህርት እድል አማራጮችና ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.