Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ የተከሰተው የሙቀት ማዕበል በብሪታንያ አውሎ ንፋስ እና ከባድ ዝናብ ማስከተሉ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በብሪታኒያ ፣ ደቡብ ዌልስ እና ደቡብ ምዕራብ እንግሊዝ የተከሰተው የሙቀት ማዕበል አውሎ ንፋስ እና ከባድ ዝናብ ማስከተሉን የሀገራቱ ብሔራዊ የሚቲዮሮሎጂ አገልግሎት ገለጸ፡፡

በተከሰተው የአየር ንብረት መዛባትም በዛሬው ዕለት በደቡብ ዌልስ እና ደቡብ ምዕራብ እንግሊዝ የጉዞ መስተጓጎል መፈጠሩ ተነግሯል፡፡

በነገው ዕለትም በደቡብ እና ምሥራቅ እንግሊዝ ተመሳሳይ ሁኔታ ሊያጋጥም እንደሚችል አናዶሉ ዘግቧል፡፡

የብሪታንያ የብሔራዊ ሚቲዮሮሎጂ አገልግሎት ኃላፊ ፓውል ጋንደርሰን ÷ በአካባቢዎቹ በሚዘንበው ከባድ ዝናብ ሳቢያ መንገዶች ውሃ ሊቋጥሩ እና ለማሽከርከር አስቸጋሪ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

በመጪው እሑድ የንፋሱ ሁኔታ እንደሚቀንስ ቢጠበቅም ካፊያ እና ዝናብ ግን በሰሜናዊ የብሪታንያ ክፍል እንደሚኖርም ነው ያመላከቱት።

በትናንትናው ዕለት የወጣው የአውሮፓ የጠፈር ኤጀንሲ መረጃ እንዳመላከተው ደግሞ ÷ በጣሊያን፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ፖላንድ የተከሰተው የሙቀት ማዕበል በመጪዎቹ ቀናት ሊቀንስ ይችላል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.