Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 3 ሺህ 942 ኩንታል ማዳበሪያ በሕገ- ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ39 ወረዳዎች በተለያየ ጊዜ 3 ሺህ 942 ኩንታል ማዳበሪያ በሕገ- ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ 259 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የ52ቱ ሰዎች 1 ሺህ 361 ኩንታል ማዳበሪያተወርሶ በየአካባቢያቸው በሚገኙ የኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል በተተመነለት ገንዘብ ለአርሶ አደሩ መሸጡ ተገልጿል፡፡

153ቱ በምክርና በማስጠንቀቂያ መታለፋቸውንና ቀሪዎቹ ጉዳያቸው ለፍርድ ቤት መቅረቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በአማራ ክልል ሕገ- ወጥ የማዳበሪያ ንግድን ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት የተገኘው ውጤት ችግሩ ሰፊ መሆኑን አመላካች መሆኑን ቢሮው አስታውቋል፡፡

ሕገ- ወጥ ድርጊቱ አርሶ አደሮች፣ ነጋዴዎች እና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዋና ተሳታፊ መሆናቸው እና “አምቡላንስ” ጭምር ለሕገ- ወጥ ሥራው አገልግሎት ላይ መዋሉ ተመላክቷል፡፡

በክልሉ ከሚገኙት 170 በላይ ወረዳዎች ይህ መረጃ የ39 ወረዳዎች ብቻ ከመሆኑ አንጻር በክልል አቀፍ ደረጃ ችግሩ ሰፊ መሆኑን ያሳያል ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.