Fana: At a Speed of Life!

የክረምት ወራት የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ሐሳብ ለሁለተኛ ጊዜ በ10 ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተከናወነው የክረምት ወራት የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናቋል።

የክረምት ወራት የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ ሥነ- ሥርዓት ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አሕመድ÷ ወጣቶቹ ባለፉት 21 ቀናት በአራቱም የሀገሪቱ ጫፍ በመጓዝ በጎነትና የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በይበልጥ ለማስረጽና በዘርፉ ንቅናቄ እንዲፈጠር ውጤታማ ስራ ማከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

ወጣቶቹ ከ8 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ በሸፈነው ቆይታቸው÷ የአረንጓዴ ዐሻራ እና የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤቶች እድሳት ጨምሮ በ13 የሥራ ዘርፎች አገልግለዋል ነው ያሉት፡፡

በተለይም ወጣቶቹ በደረሱበት ቦታ ሁሉ ስለሰላምና የሕዝቦች አብሮነት ሠርተዋል ነው ያሉት፡፡

በቀጣይም ከወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ወደ ድንበር ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማሳደግ ሚኒስቴሩ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

በጎህ ንጉሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.