Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተከናወነ።

በተለያዩ ሀገረ ስብከት የሚመደቡ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ናቸው የተሾሙት።

የኤጲስ ቆጶሳቱ ሹመት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ መሪነት በመንበረ ፓትሪያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተፈፅሟል።

በዚህ መሰረት ፡-

1. አባ ክንፈ ገብርኤል ተ/ማርያም አባ ገሪማ ተብለው የጌዲኦ፣ አማሮና ቡርጅ ሀገረ ስብከት፣

2. አባ ሳህለ ማርያም ቶላ አባ ገብርኤል ተብለው የምዕራብ ሸዋ ሀገረስብከት፣

3. አባ ስብአት ለአብ ሀይለማርያም አባ ጢሞቲዎስ ተብለው የዳወሮ ኮንታ ለገረ ስብከት፣

4. አባ አምደሚካኤል ሀይሌ አባ ኤልሳዕ ተብለው የምስራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት፣

5. አባ ሀይለማርያም ጌታቸው አባ በርቶሎሜዎስ ተብለው የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት፣

6. አባ ጥላሁን ወርቁ አባ ኤፍሬም ተብለው የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት፣

7. አባ ዘተ/ሀይማኖት ገብሬ አባ ኤጲፋንዮስ ተብለው የሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት፣

8. አባ እስጢፋኖስ ገብሬ አባ ዳንኤል ተብለው የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት እና

9. አባ ወ/ገብርኤል አበበ አባ ኒቆዲሞስ የምስራቅ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት ሆነው ተሹመዋል።

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.