Fana: At a Speed of Life!

“አረንጓዴ አሻራ ጉልበታችንን፣ አብሮነታችንንና ሀገራዊ ጥንካሬያችንን መፍጠር የቻልንበት ነው” – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) “አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በሀገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ በነበሩ ፈተናዎች ውስጥ ሆነንም ጉልበታችንን፣ አብሮነታችንንና ሀገራዊ ጥንካሬያችንን መፍጠር የቻልንበት ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገለግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ 500 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምበር የመትከል መርሐ ግብርን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ሁነት ከማለዳው 12 ሠዓት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ወደተዘጋጁ የችግኝ መትከያ ቦታዎች እያመሩ እንገሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ንጹህና ተስማሚ አየር እንዲሁም ለኑሮ ተስማሚ ሀገርን ለመፍጠር የአረንጓዴ አሻራ ዋነኛ አላማውን አድርጎ ባለፉት 4 አመታት ሲተገበር ቆይቷ ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.