በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ተጀምሯል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ተጀምሯል፡፡
መርሐ ግብሩ ከማለዳው 12 ሠዓት ጀምሮ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተጀምሯል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ነዋሪዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።