በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ችግኝ የመትከል መርሐ-ግብሩ ማለዳ ነው መካሄድ የጀመረው፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በመርሐ-ግብሩ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በክልሉ የተለያዩ ዞን፣ ወረዳና ቀበሌ ነዋሪዎች በመርሐ-ግብሩ ላይ በመሳተፍ አረጓንዴ አሻራቸውን በማኖር ላይ እንደሚገኙ ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡