አቅምና ጉልበት ያለው ሁሉ ኢትዮጵያን የማልበስ ኃላፊነት ሊወጣ ይገባል – አቶ ርስቱ ይርዳ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አቅምና ጉልበት ያለው ሁሉ ኢትዮጵያን የማልበስ ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ርዕስቱ ይርዳ ገለጹ፡፡
500 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀንበር የመትከል መርሐ ግብር የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን እየተካሄደ ነው፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር፥ የሚተከሉት ችግኞች ለሕብረተሰቡ ፈርጀ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) በበኩላቸው÷ አረንጓዴ ዐሻራ ማስቀመጥ ከትውልድ ትውልድ የሚሻገር ቅርስ ማስቀመጥ ስመሆኑ አስገንዝበዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው÷ ዘር ብዙ ጥቅም ያላቸውን ችግኞች በመትከል የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡
በዛሬው ዕለት እየተተከሉ ከሚገኙት ችግኞች መካከል÷ የደን፣ የጥምር ደን፣ ቀርከሃ፣ ፍራፍሬ እና የእንስሳት መኖ ይገኙበታል፡፡
በኢብራሂም ባዲ፣ መለሠ ታደለ እና ጥላሁን ይልማ