Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል የ2015 የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት የ2015 ዓ.ም የመንግሥት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተጀምሯል፡፡
በግምገማው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በዚሁ ወቅት÷ግምገማው ጊዜን በመቆጠብ ስራዎች በአግባቡና በሚገባ እንዲመዘኑ ይረዳል ብለዋል፡፡
የአመራሩ ግምገማና የመስሪያ ቤቶች አፈፃፀም ሪፖርት በአመት አንዴ የሚካሄድ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው አመራሩ በተሰጠው ስራ መሰረት በመገምገም ምዘናዎች ተካሂደዋል ብለዋል።
በግምገማው “በአንድ ፕላን አንድ ሪፖርት” መርህ አማካኝነት የየመስሪያ ቤቶቹ እቅዶች እየተመዘኑ እንደሚገኙ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ከምዘናው በኋላም የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት እና የክልሉ የክትትልና ቁጥጥር ሪፖርት እንደሚቀርብ ተጠቁሟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.