ኢትዮጵያ የምታከናውነው የአረንጓዴ አሻራ ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ ያስችላል – ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) የብሪታኒያ – አፍሪካ የሚኒስትሮች ፎረም ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡
በፎረሙ የኢትዮጵያ የማዕድን ሃብትና የኢንቨስትመንት አማራጮች መቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም ሚኒስትሩ ፥ መንግስት ለማዕድን ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ መዋዕለ ንዋያቸውን በዘርፉ ለሚያፈሱ አቅም፣ ፍላጎትና ልምድ ላላቸው ባለሃብቶች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የምታከናውነው የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በማጎልበትና ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከብሪታኒያና ሌሎች የልማት አጋር ተቋማት ጋር በዘርፉ ለምታከናውናቸው የልማት ተግባራት የዕውቀት፣ የክህሎት፣ የቴክኖሎጅ ሽግግርና በፋይናንስ ተደራሽነት በትብብር እንደምተሰራም አረጋግጠዋል፡፡