በአማራ ክልል 1 ሺህ 34 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ2015 በጀት አመት 4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የደረገባቸው 1 ሺህ 34 አዳዲስና ነባር ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን የክልሉ ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ገለፀ።
በክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በሰላም ይመኑ፥ በተያዘው አመት ተጀምረው ግንባታቸው እስከ ሐምሌ 30 ቀን የሚጠናቀቁ ነባር እና አዳዲስ ፕሮጀክቶች ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡
በክልሉ በ32 ከተሞች በዓለም ባንክ፣ በመንግስት በጀት እንዲሁም በህዝቡ ተሳትፎ 4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ህዝብን በተግባር ማሳተፍ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ጠቅሰው፥ ከተሞችን ማልማት ላይ ተሞክሮ የተወሰደበት ነውም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በእሸቱ ወልደሚካኤል