Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአቅመ ደካሞች 133 የመኖሪያ ቤቶች ቁልፍ አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአስከፊ ችግር ውስጥ ለሚገኙ የሃገር ባለውለታዎች፣ አቅመ ደካሞች እንዲሁም ለአካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች 133 የመኖሪያ ቤቶች ቁልፍ አስረከቡ።

በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ ከንቲባዋ እንዳመለከቱት፤ ቤቶቹ ያለ አግባብ ተይዘዉ የነበሩ ናቸው።

ህብረተሰቡን በማሳተፍ ቤቶቹ እንዲመለሱ እና ለሚገባቸው ነዋሪዎች እንዲሰጥ መደረጉን መግለጻቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.