Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በተመድ የተያዙ የዘላቂ የልማት ግቦችን እያሳካች ነው – አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተያዙ የዘላቂ የልማት ግቦችን እያሳካች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው የተመድ ከፍተኛ የፖለቲካ መድረክ የዘላቂ የልማት ግቦች ዕቅድ አፈፃፀም ላይ በኢትዮጵያ የተመዘገበውን እድገት አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ÷ኢትዮጵያ በተመድ የተያዙ ዘላቂ የልማት ግቦች እንዲሳኩ ከአገራዊ በጀቷ ከፍተኛውን ድርሻ ለዘላቂ ልማት ግቦችና ለድህነት ተኮር ፖሊሲዎች፣ ለአየር ንብረት ዘርፍ በመመደብ ለልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ልዩ ትኩረት በመስጠት ቁርጠኛ መሆኗን አመልክተዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦች አፈፃፀም ዙሪያ በሚመክረው መድረክ አገራት በተያዘው እቅድ መሰረት ተግባራት እና ግቦችን መፈፀማቸው ይገመገማል ።

እንደ በፈረንጆቹ 2030 የሚጠናቀቀው የዘላቂ ልማት ግቦች እቅድ በኢትዮጵያ በውሃ ፣በአካባቢ ንፅህና ዘላቂ እና ተመጣጣኝ ኃይል አቅርቦት፣ መሠረተ ልማት እንዲሁም የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት ዘርፎች የተሰሩ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸው ተገልጿል።

የከፍተኛ ደረጃ ፖለቲካ መድረኩ ሀገራት የተቀመጡትን ግቦች አፈፃፀም ደረጃ ያቀረቡበት፣ልምድ የሚለዋወጡበት እና እርስ በእርስ የሚማማሩበት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

አምባሳደር ምስጋኑ ከዚህ መድረክ ጎን ለጎን ከዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ካትሪን ራስል ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.