የሽግግር ፍትሕን አስመልክቶ ለአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ገለጻ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽግግር ፍትሕን አስመልክቶ ለአውሮፓ ህብረትና አባል ሀገራት ተወካዮች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማብራሪያ ተደርጓል፡፡
ማብራሪያውን የሰጡት የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፖለቲካ አማካሪ አምባሳደር ሚኒልክ አለሙ ናቸው።
በገለፃው ላይ በዋናነት የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እና አባል ሀገራት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን (ዶ/ር) በሽግግር የፍትህ ፖሊሲ አማራጮች አፈፃፀም እና የተከናወኑ ተግባራት ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የሽግግር ፍትህ የፖሊሲ አማራጮች የስራ ቡድን አደረጃጀትን በሚመለከት፣ በቡድኑ የተቀረፀውን የሽግግር ፍትህ የፖሊሲ አማራጮችን እና በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እስካሁን ከባለድርሻ አካላትና ከአጋር አካላት ድጋፍ ጋር የተካሄደውን ልዩ ልዩ ህዝባዊ ምክክርን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የቀጣይ የአፈጻጸም ዕቅዶች በተመለከተም ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡