Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ተመዝብሮ የነበረ 35 ሚሊየን ብር እና ከ17 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ መሬት እንዲመለስ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ተመዝብሮ የነበረ 35 ሚሊየን ብር እና 17 ሺህ 500 ካሬ ሜትር መሬት ማስመለስ መቻሉን የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ቢሮ ሃላፊ አቶ አዩብ አሕመድ እንዳሉት÷ በክልሉ በመንግስት ተቋማት ለሙስና እና ለመልካም አስተዳደር መበላሸት ምክንያት የሆኑ ችግሮችን በመለየት በትኩረት ተሰርቷል።

በዚህ መሰረትም በመሬት ነክ ጉዳዮች፣ በገቢና ታክስ፣ በፍትሕ፣ በፕሮጀክቶች እና ግዢ ዘርፎች ላይ በትኩረት መሰራቱን ነው የገለጹት፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ምርመራቸው ተጠናቆ ለፍርድ ቤት ከቀረቡት 1 ሺህ 374 መዛግብት ውስጥ 720ዎቹ ላይ ውሳኔ መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡

ከሙስና ጋር በተያያዘ መንግስት ሊያጣው የነበረ ከ35 ሚሊየን ብር በላይ ማስመለስ መቻሉን አቶ አዩብ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በሕገ-ወጥ መንገድ በግለሰቦች ተይዞ የነበረ 17 ሺህ 500 ካሬ ሜትር መሬት እንዲመለስና ወደ መንግስት መሬት ባንክ ገቢ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

የሕዝብ ሃብትን በክስና በድርድር ከማስመለስ አንጻርም 22 ሚሊየን ብር በላይ በድርድር ማስመለስ መቻሉንም አስረድተዋል።

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.