Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ ቀጣይ ምርጫን በተመለከተ በሚቀርቡ የመፍትሄ አማራጮች ላይ ነገ ይወያያል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ልዩ ስብሰባውን ነገ ሚያዝያ 27 እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫን በተመለከተ የቀረቡ የመፍትሄ አማራጮችን የውሳኔ ሃሳብ እና ስድስት የብድር ስምምነቶችን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው ያስታወቀው።

ምክር ቤቱ ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባው ለህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫን በተመለከተ የቀረቡትን የመፍትሄ አማራጮችን መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ እንዲቀርብ መመራቱ የሚታወስ ነው።

በመሆኑም ምርጫን በተመለከተ ከቀረቡ አራት የመፍትሄ አማራጮች መካከል ቋሚ ኮሚቴው መርምሮ የሚያቀርበው የውሳኔ ሃሳብ ነገ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.