አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቢኒያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ የክብር ዶክትሬት ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቢኒያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።
ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በማታና በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 8 ሺህ 642 የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን በሚሊኒየም አዳራሽ እያስመረቀ ነው።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
በስነ-ሥርዓቱ ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ የክብር ዶክትሬት ማበርከቱን የዘገበው ኢዜአ ነው።
እንዲሁም ለአርቲስት ደበበ እሸቱ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።
አርቲስት ደበበ በስነርዓቱ ላይ ተገኝቶ የክብር ዶክትሬቱን ተቀብሏል።
አርቲስት ደበበ እሸቱ በኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ያለው ሲሆን÷ ለዚህም የተለያዩ እውቅና አግኝተዋል።