አሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች እና የዳያስፖራዎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ አስመልክቶ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውይይት ተካሄደ።
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እንድሪስ(ዶ/ር) አወያይተዋል።